‘ human beings are MANKINDs greatest asset’

Dr. Zumra Nuru

Awra Amba Community

Awra Amba intentional society has just celebrated its fiftieth years of formation in April 2022 under its iconic leader Zumra Nuru, who lead 66 peasant and youth forces to set up a community with five famous major principles in mind:

caption

Gender equality

In der Schule von Awra Amba

children´s rights

IMG_1020

good deeds &
good speech

8d29554c1c9fd536e5e4ed742cea690b

compassion & care
for the elderly

But there was a universal principle which bound all these four principles together and which was not stated explicitly: 

At the center of the universe and society should be human beings and their universal rights.

Any social, economic system that does not start from the principle of meeting human needs and unconditionally respecting rights as its central and organizing principle, should be recast to reflect this.

All human beings should be welcomed to the community as members irrespective of ethnicity, race, creed & religion, language, social class or any other form of labeling and classifying people that undermines the universal brotherhood and sisterhood of humanity.

What is so earthshaking about these principles of human solidarity was the fact that these bunch of 18 people were not intellectual zealots bent on changing the world. Zumra himself did not have a days schooling and could neither read or write and his fellow travelers were all of peasant origin with tilling the land as their main means of livelihood. 

With unabashed lack of modesty they took on the daunting task of setting up a new human centered world and creating a society of pioneers with no capital or intellectual stock or political organization to their fame.

The 18 pioneers were soon confronted with one big issue:

How do they make money when they had such little land for agricultural  production?

The answer was to develop a trade skill…

Soon the members undertook a training in weaving.

To make a long story short the wooden looms were eventually replaced by metal ones and this small scale industry became so succesfull that it trained whole generations of weavers. 

Awra Amba has now the greatest concentration of garment cottage industries realtive to total population.

Since its founding some 50 years ago, this intentional society has spread its activities and institutions and as the following pages show some of the main projects , there are now some 48 areas of activity.


WELCOME TO AWRA AMBA. 

የአውራ አምባ ማህበረሰብ በአጭሩ

የክብር ዶ/ር ዙምራ ኑሩ የአውራ አምባ ማህበረሰብ መስራች ሲሆን በሁለት ዓመት ዕድሜው እንደትልቅ ሰው የመናገርና የመጠየቅ ብቃት ያገኘ ሀያልና ባለብሩህ አእምሮ ባለቤት ነው፡፡ ከአራት ዓመት ዕድሜው ጀምሮ በአካባቢው መሰራት እሚገባቸው በጎ ነገሮች ሳይሰሩ ቀርተው መሰራት እማይገባቸው መጥፎ ነገሮች ሲሰሩ በመመልከቱ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ሀሳቦችን አንስቷል፡፡ መሰረታዊ ጥያቄዎቹና ሀሳቦቹም የሴቶችን እኩልነት ማክበር፣ የህጻናትን መብት ማክበር፣ የወደቁ ወገኖችን መደገፍ፣ መጥፎ አሰራርና አነጋገርን ማስወገድ በሚሉ ጥቅል ሀሳቦች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡ እሱ እነዚህን መሰረታዊ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ከማንሳቱም ባሻገር ከውልደቱ ጊዜ ጀምሮ በእሱ ላይ ህይወቱን የፈተኑ በርካታ የተለያዩ አጋጣሚዎችና ታምራዊ ክስተቶች ተከስተው አልፈዋል፡፡

 

    የክብር / ዙምራ በዚህ የለጋነት ዕድሜው እነዚህን ጥያቄዎችና ሀሳቦች ሲያነሳ ከሚኖርበት የማህበረሰብ ክፍል ውስጥ ጥያቄዎቹን ለመመለስም ሆነ ሀሳቦቹን ለማዳመጥ ጆሮ የሰጠው ሰው አልነበረም፡፡ የማህበረሰብ ክፍሎቹ እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎችና ሀሳቦች ሲነሱ አስተውለው ስለማያውቁ የሚያነሳቸውን ሀሳቦች ትኩረት ሰጥተው ከመከታተል ይልቅ አስተሳሰቡ ከእነሱ አስተሳሰብ ጋር ስላልገጠመላቸው “ይኸ ልጅ ይህን እሚናገረውና እሚጠይቀው የአእምሮ ችግር አግኝቶት ታምሞ (አብዶ) ነው” የሚል ፍረጃ ሰጡት፡፡ እሱም ሌላ አማራጭ ስለሌለው “እብድ” ተብሎ የተሰጠውን ፍረጃ በመሸከም ባይተዋር ሆኖ በእረኝነትና በሌሎች የተደራረቡ ስራዎች ጫና ላይ ወድቆ በሀሳብ በመብሰልሰል የህጻንነት ጊዜውን ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ እስከ አስራ ሁለት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ማሳለፍ ግድ ሆኖበታል፡፡

 

    አስራ ሶስት ዓመት ሲሞላው በዓይኑ እሚያየውና በጆሮው እሚሰማው አእምሮውን የበለጠ እረፍት እየነሳው ሲመጣና መፈጠሩን እየጠላ ሲሄድ ከሚኖርበት አካባቢ ወጣ ብሎ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች የሚመልስለትና ሀሳቡን የሚቀበለው ህብረተሰብ ፍለጋ ጎንደር፣ ጎጃምና ወሎ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ እሚበላ፣ እሚጠጣና እሚለበስ በሌለበት ሌሊት በእዛፉ ስር ጠጋ ብሎ በዱር አራዊቶች ተከብቦ እያደረ ሀሩሩን፣ ቁሩንና ረሀቡን ተቋቁሞ ያውቃሉና ትልልቅ ለሚባሉ ሰዎች ጥያቄዎቹን እያቀረበ ለአምስት ዓመታት ያህል ሰፊ ጥናት ሲያደርግና ሀሳቦቹን ሲገልጽ ቆዬ፡፡

 

    ሀሳቡን እሚገልጥላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም ተወልዶ እንዳደገበት የህብረተሰብ ክፍል “ታምሞ! (አብዶ!) ባይሉትም “ይቺ ልጅ ምን ማለቷ ነው? እምታነሳው ሀሳብ ትክክለኛና መልዕክት ያለው ነው፡፡ ግን ማን ይወስደዋል ብላ ነው? እያሉ በግርምት ከማየት በስተቀር ሀሳቡን እሚረዳለትና እሚካፈለው አካል አላገኘም፡፡

 

    በተንቀሳቀሰባቸው /ሀገሮች ሀሳቡን እሚካፈለው የህብረተሰብ ክፍል ሲያጣ “እንግዲህ ወደ አገር ቤት ልመለስና ወላጆቼ እንደሚሰሩት እየሰራሁና በአካባቢው ያሉ ደካሞችን እየረዳሁ ብኖር ትንሽ የህሊና ረፍት አገኝ ይሆናል” ብሎ በማሰብ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት በመመለስ ወላጆቹን “ትዳር ልይዝ ነው ሴት ፈልጉልኝ” አላቸው፡፡ እነሱም “በአእምሮ ችግር አብዶ፣ ታሞ፣ ከቦታ ቦታ እየዞረ” ሲሉ የነበሩት “ትዳር ካሰበ በሽታው ለቆት ነው፡፡ በሽታው ባይለቀው ኖሮ ትዳር አያስብም ነበር” የሚለውን በማሰብ ደስ ብሏቸው ወዲያው ሴቷን ፈልገው ትዳሩን እንዲመሰርት አደረጉ፡፡ እሱም ትዳሩን መስርቶ እንደ ወላጆቹ እርሻ እያረሰና በሌሎች ስራዎች ተሰማርቶ በየዓመቱ የሚያገኘውን ምርት በአካባቢው ለሚገኙ ደካሞች ማከፋፈል ጀመረ፡፡ ይህን ሲያደርግ ቤተሰቦቹ ለእሱ በማሰብ “አይ ይኸ ልጅ አይድንም፤ የሚድን በሽታም አይደለም የያዘው፡፡ እሱ አይበላም፣ አይጠጣም፣ አይለብስም፣ ለዚህ አልታደለም፡፡ የሱን ገንዘብ ዘመድ አያገኘውም፡፡ ዝም ብሎ ለባዕድ ነው እሚሰጠው” አሉ፡፡

 

       እዚህ ላይ ለእሱ ከፍተኛ ግርምትን ፈጠረበትና “ከሰው ልጆች መካከል ባዕዱ ማን ነው? ባዕድ እምትሉት የትኛውን ነው? ዘመድ እምትሉትስ? በኔ በኩል ሰዎች በሰውነታችን የአንድ አዳምና ሄዋን ልጆች የአንድ ሀረግ ፍሬዎች ነን፡፡ የአዳም ዘር ሳይቀየር ባዕድነት በየት አልፎ ገባ? የሚል ጥያቄ አነሳ፡፡ ይህን በሚጠይቅ ጊዜ “አሞህ እኮ ነው ባዕድና ዘመድ መለየት ያቃተህ፡፡ አንተ ሁሉን ዘመድ አድርገህ የምትኖረው አሞህ ነው፡፡ ብታውቅ! ከሰባት ትውልድ በኋላ ያለው ሁሉ ባዕድ ነው” አሉት፡፡ ይህን ሲሉት ሌላ ተጨማሪ ግርምት ተፈጠረበትና “ሰባት ትውልድ ከደረሳችሁ በኋላ ባዕድነት ትፈጥራላችሁ ያለው ማነው? እንዲህ እያልን ባዕድነትን እንፈጥራለን፡፡ ባዕድነት ጥላቻን፣ ጥላቻ ጠብን፣ እየፈጠረ ሰውን ሰው እንደ አውሬ እየፈራነው እምንሄደው እኛው እምንስለው ነው፡፡ እህቴ ወንድሜ ብለን ብንሄድ ኖሮ ልዩነት ባልሰፋ ነበር፡፡ ሁሉም የሰው ልጆች ሰው በመሆናችን ብቻ ወንድም እህት መሆን አለብን፡፡ ለዝምድና ሰው ሆኖ መገኘት ብቻ በቂ ነው” በማለት አምስተኛውን መሰረታዊ ሀሳብ አነሳ፡፡

 

    ይህን አምስተኛውን መሰረታዊ ሀሳብ ሲያነሳ መሰረታዊ ሀሳቦቹን ከአራት ወደ አምስት ከፍ አደረጋቸው፡፡ እነዚህን አምስት ጥቅል መሰረታዊ ሀሳቦችም ባለው አቅም ሁሉ በስራ ላይ ሲያውላቸው ቆዬ፡፡ ሆኖም ይህን በውጤታማነት ለመቀጠል አጋር አካላት እስካላገኘ ድረስ እንደማይሆንለት ያውቀዋልና እርሻ በማያርስበት በበጋው ወቅት ተስፋ ባለመቁረጥ “ምናልባት ሀሳቤን የሚጋራኝ ህብረተሰብ ባገኝ” እያለ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሱን ቀጠለ፡፡

 

    እርሻ በማያርስበት በበጋ ወቅት በአንዱ ቦታ ሄዶ ሀሳቡን የሚጋራው ህብረተሰብ ሲያፈላልግ ይቆይና የእርሻ ወቅት ሲሆን ደግሞ ይመለሳል፡፡ እንዲህ እያለ ያለማቋረጥ ለበርካታ ዓመታት ያክል ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ የሃሳቡ ተጋሪ ማህበረሰብ ለማግኘት እልህ አስጨራሽ ጥረት ሲያደርግ ቆይቶ ደቡብ ጎንደር ፎገራ ወረዳ ላይ በገበሬዎች ዙሪያ ሀሳቡን የሚያዳምጡ ሰዎችን አገኘ፡፡ ገበሬዎቹ ሀሳቡን ትኩረት ሰጥተው ስላዳመጡት በየዓመቱ እየተመላለሰ ከእነሱ ጋር በጥቅል መሰረታዊ ሀሳቦች ዙሪያ በርካታ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆዬ፡፡ ሀሳቡን ያካፍላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም ሀሳቡን ወድደው ተቀበሉት፡፡ ሀሳቦቹ ተቀባይነትን ሲያተርፉለት “እንግዲህ ከእነሱ ጋ ሄጄ ብቀመጥ እቅዴ ሊሳካ ይችላል” በማለት ሲኖርበት የነበረውን እስቴ ወረዳ ለቅቆ ገበሬዎቹ ወደ እሚገኙበት ፎገራ ወረዳ በማምራት በ1964 ዓ.ም የአውራ አምባ ማህበረሰብን መሰረተ፡፡

 

   የክብር / ዙምራ የአውራ አምባ ማበረሰብን ከመሰረተ በኋላ ያነሳቸውን መሰረታዊ ሀሳቦች ለመሰረተው ማህበረሰብ አባላት በጥልቀትና በስፋት በማቅረብ ከራሱ የህይወት ተሞክሮ ጋር በማዛመድ እሱ ሲሰራቸው የቆየውን ምሳሌነት ያላቸው ተግባራት በመጠቀም ለሰው ልጆች የሚኖራቸውን ጠቀሜታና እንዴት በስራ ላይ መዋል እንደሚችሉ በሰፊው በማስረዳት ሀሳቦቹን ለማስረጽ ከፍተኛ ጥረት አደረገ፡፡ አባላቱም በተበታተነ መልኩ ሆነው በያሉበት መሰረታዊ ሀሳቦቹን ለመተግበር በሰፊው ተንቀሳቀሱ፡፡ ሆኖም በተበታተነ መልኩ ሆነው ኑሯቸውን መቀጠላቸው ሀሳቦቹንና መርሆዎችን በተቀናጀ መልኩ ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ምቹ አልሆነለትም፡፡ ስለሆነም  ማህበረሰቡን ከተበታተነ ኑሮ ወደ (አብሮነት) ኑሮ ማሸጋገር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኖ አገኘው፡፡

    የክብር / ዙምራ የአብሮነት ኑሯቸውን ለመጀመር እንዲያስችላቸው አባላቱን ከነሀሴ 1-ጳጉሜ 5 1976 . ድረስ እንደገና በአዲስ መልክ በመሰብሰብ ጥልቅ የሆነ የውይይትና የምክክር መድረክን ከፍቶ ሀሳቦቹን በደንብ እንዲረዱ ሰፊ ማብራሪያ ሲሰጣቸው ቆዬ፡፡ በዚህ የውይይት መድረክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ለሰው ልጆች ሰላማዊና ምቹ ኑሮን ለመመስረት ያስኬዱናል ብሎ ያመነባቸውን መርሆዎች ለይቶ በማውጣት አወያያቸው፡፡ አባላቱም እሱ ያቀረበላቸውን መርሆዎች ጊዜ ሰጥተውና በትኩረት ሲከታተሉ ቆይተው ሁሉንም በስራ ላይ ለማዋል በአንድ ድምጽ ተስማምተው በማጽደቅ የአብሮነት ኑሯቸውን ለመጀመር ወሰኑ፡፡

 

    እሱ የመሰረተውን ማህበረሰብ በአዲስ አስተሳሰብ በማነጽ መጥፎ አሰራርና አነጋገርን አስወግዶ በምትኩ መልካም አስተሳሰብና አሰራርን በመዘርጋት በሰው ልጆች መካከል መተሳሰብ፣ ፍቅር፣ መረዳዳትና ሰላም እንዲሰፍን እየታተረና የአብሮነት ኑሯቸውን ለመጀመር ዝግጅቱን ባጠናቀቀበት ወቅት ይህ መልካም አሰራርና አስተሳሰብ ያልተዋጠላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እሱ በሌለበትና በማያውቀው ወንጀለኛ እንደሆነ አድርገው በመክሰስ ከመስከረም 7 እስከ የካቲት 30/1978 ዓ.ም ድረስ ወረታ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንዲቆይ ቢያደርጉም የቀሩት አባላት እሱ በሰጣቸው ሀሳብ መሰረት ገና ከእስር ቤት ሳይወጣ የካቲት 6 አንድ ላይ ተሰባስበው “ሁሉም ሀብትና ንብረት የሁሉም” የሆነ የህብረት ስራ ማህበር አቋቁመው የአብሮነት ኑሮአቸውን ጀመሩ፡፡

 

   የክብር / ዙምራም ከእስር ሲፈታ እሱም የማህበር አባል ሆኖ ከሌሎቹ አባላት ጋር አንድ ላይ በመሰባሰብ መጥፎ አካሄዶችን ወደ ኋላ እያሉና መልካም አካሄዶችን ደግሞ ሳይሸራርፉ ወደ ፊት እያራመዱ በመተሳሰብ፣ በመረዳዳት፣ በመተዛዘን፣ በመተባበር፣ በፍቅርና በመተማመን በጋራ እየሰሩ የሚያገኙትንም አንተ ትብስ፣ አንቺ ትብሽ እየተባባሉ በመቃመስ የፍቅር፣ የሰላም፣ የመከባበርና የአንድነት ኑሯቸውን ቀጠሉ፡፡ ይህ መልካም አስተሳሰብና አሰራር ያልተዋጠላቸው በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች በክብር / ዙምራና በመሰረተው ማህበረሰብ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በመቀጠል መኖሪያ ቢያሳጧቸውም ሀሳቦቹን ወደ ተግባር ቀይረው ለተማሩ ሰዎች (የሀይማኖት አባቶችና የቀለም ምሁራን) ለማድረስ ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገው ሲታገሉ ቆዩ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም በእነሱ አቅም እነክብር / ዙምራን ማስለቀቅ ሲያቅታቸው 1980 . እሱን እንደለመዱት ከፖለቲካው ጋር አጋጭተው ለደርግ መንግስት ሪፖርት አደረጉ፡፡ ደርግ ደግሞ እሱን ሊያጠፋው ሲያስብ ከጥፋት ለማምለጥ ጥቂት ሰዎችን ይዞ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተሰደደ፡፡

 

   ስደት ባለበት ስራ የለም፡፡ ስራ በሌለበት ገንዘብ የለም፡፡ እሚበላ እሚጠጣም የለም፡፡ ቢታመሙ እሚታከሙበት ገንዘብ የላቸውም፡፡ በዚህም ሳቢያ የሞቱ ወገኖቻቸውን በየቁጥቋጦው ስር አፈር እያለበሱ ሀሳባቸውን ለተማሩ ሰዎች ለማድረስ ትግላቸውን ቀጠሉ፡፡ የገጠሟቸውን ውስብስብ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችንም የክብር ዶ/ር ዙምራ በሚዘይዳቸው የተለያዩ ዘዴዎች እንዲፈቱና ረሀቡንም ሳይሰማቸው ፍቅራቸውን ተመግበው እንዲያልፉ ማድረግ ስለቻለ ያሉባቸውን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየቀረፉ ሄዱ፡፡

 

    የክብር / ዙምራ ሀሳቦቹንና ተሞክሮዎቹን ተሰድዶ ለቆየበት የአካባቢው ህብረተሰብ እያስተላለፈ አምስት ዓመት ከአምስት ወር ያህል በስደት ቆየ፡፡ በዚህ ቆይታው አንዳንድ ጥሩ ነገር እማይዋጥላቸው ግለሰቦች እሱን ለማጥፋት ከመታገል ባይቆጠቡም እሱ ለእነዚህ ለሚታገሉት ግለሰቦች ጭምር በጎ እያደረገላቸውና በአብዛኛዎቹ የአካባቢው ህብረተሰብ ክፍሎች ተወዳጅነትን በማትረፍ ከነሀሴ ወር 1985 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር መጨረሻ 1986 ዓ.ም ድረስ አባላቱን ይዞ ወደ አውራ አምባ ተመለሰ፡፡ 

 

    ወደ አውራ አምባ ሲመለስ ለስደት የዳረጓቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በጥሩ እይታ አልተቀበሉትም፡፡ መሬታቸውንም ይዘው አናስነካም አሉ፡፡ እሱም ትዕግስት በተሞላበት ሁኔታ መሬታቸውን ለማስመለስ ለወረዳ፣ ለዞንና ለክልል ቢያመለክትም ወረዳው በ1987 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ለቤተ-ቦታ የሚሆን ብሎ 17.5 ሄክታር መሬት ብቻ ሰጣቸው፡፡ እሱም ተጨማሪ የእርሻ መሬት እንዲሰጣቸው ደጋግሞ መጠየቁን ቢቀጥልም ተጨማሪ መሬት ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ በወቅቱ በማህበረሰቡ ከ260 በላይ የሚሆኑ የቤተሰብ አባላትን ያቀፉ ከሰባ በላይ አባዎራዎችና እማውራዎች ነበሩ፡፡ ይቺ የተሰጠቻቸው መሬት መኖሪያ ቦታቸውን ጨምሮ ለእርሻ የምትበቃ ስላልሆነች ኑሯቸውን የሚመሩበት ስራ አላገኙም፡፡ ከዚያም በላይ ሀሳባቸውን ያልተገነዘቡት የአካባቢው ነዋሪዎች እነሱን ማሳደዳቸውን ቀጥለውበታል፡፡

 

 የማህበረሰቡ አባላትም የአካባቢው ህብረተሰብ ካለማወቅ በሚሰነዝርባቸው የማሳደድ ዘመቻና የስራ እጦት ምክንያት በረሀብና በበሽታ ለስቃይና ለእንግልት ተዳርገው የመኖር አለመኖር ትግላቸውን ሲቀጥሉ በርካታ የማህበረሰቡ አባላት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ የማህበረሰቡ አባላት በዚህ ሁኔታ ሀሳባቸውን ባልተረዱ የአካባቢው ነዋሪዎች አሳደህ አጥፋው ተብሎ እንደተፈረደበት የዱር አውሬ ተሳደው እንዲጠፉ ተመክሮባቸው እየተሳደዱ ማህበረሰቡ ከተመሰረተበት ከ1964 ዓ.ም ጀምሮ ሶስት አስርት ዓመታትን በአሰቃቂ ሁኔታ በማሳለፍ ሀሳባቸውን ለተማሩ ሰዎች ለማድረስ ከባድ መስዋእትነትን ሲከፍሉ ቆዩ፡፡ ይህንን ሁሉ ግፍና መከራ አልፈው በ1993 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት የሚዲያ ሽፋን ስለሰጣቸው በኢትዮጵያ ብሎም በዓለምአቀፍ ደረጃ እንዲታወቁና ከተማሩ ሰዎች ጋር እንዲገናኙ በር ተከፈተላቸው፡

      የክብር ዶ/ር ዙምራም ሀሳቡ ሚዲያ ላይ መዋል ሲጀምር “ወይ እሚሰማኝ ወይ እሚጠይቀኝ ባገኘሁ” ብሎ ከልጅነቱ ጊዜ ጀምሮ ያጣውን የሚሰማኝ (ሀሳቤን በተግባር የሚያውል) ሰው አገኘሁ ለማለት ባይችልም ሀሳቡን እሚረዳለት ሰው በማግኘቱ አንድ እርምጃ ብሎ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉ ሰዎች ሀሳቡን በመጽሄት፣ በጋዜጣ፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በኢንተርኔት እያገኙና እቦታው ድረስም እየመጡ እየተረዱለት ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው የአውራ አምባ ማህበረሰብ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ታውቆና ተረጋግቶ ለመኖር የጀመረው፡፡ ማህበረሰቡ ተረጋግቶ መኖር ሲጀምር “ህይወት የተንጠለጠለው በመሬት ብቻ አይደለም በኢንዱስትሪም ማደግ ይቻላል” በማለት ወደተለያዩ የስራ ዘርፎች በመግባት የተደራረቡበትን ውስብስብ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል አሁን ላይ ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት ላይ ይገኛል፡፡   

    የአውራ አምባ ማህበረሰብ ሁለት ዓይነት የአባልነት ደረጃዎች አሉት፡፡ እነሱም የአውራ አምባ ማህበረሰብ አባልና የአውራ አምባ ሁለገብ ኅብረት ስራ ማህበር አባል ናቸው፡፡ የማህበረሰብ አባል ሲባል በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነው በተናጠል በግላቸው የሚኖሩትንም ሆነ በማህበር ተደራጅተው አንድ ላይ በጋራ እየሰሩ የሚኖሩ አባላትን የሚያካትት ሲሆን ማህበረሰቡ የሚመራባቸውን እሴቶችና መርሆዎች በማወቅ፣ በመተግበርና እሴቶቹንም ወደ ሌላው የህብረተሰብ ክፍል እንዲስፋፉ በማድረግ ለማህበረሰቡ ደንብ ተገዥ ሆነው የሚኖሩትን ያጠቃልላል፡፡ የማህበረሰቡ ራዕይም ሁሉም የሰው ልጆች ወንድም እህት ሆነው እርስ በርሳቸው ተከባብረው፣ ተሳስበው፣ ተረዳድተውና ተፈቃቅረው የሚኖሩበት ዓለም ተፈጥሮ፣ ድህነት ከዓለማችን ጠፍቶ፣ ሁሉም የሰው ልጆች ስለሰላም ሲያስቡና ቀጣይነት ያለው ሰላም በሁሉም የዓለም ክፍል ላይ ተዘርግቶ የሰው ልጆች በሙሉ እፎይ ብሎ የሚኖሩበት ዓለም ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡

   የህብረት ስራ ማህበር አባላት ደግሞ የአውራ አምባ ማህበረሰብ አባል ከሆኑት ግለሰቦች መካከል በራሳቸው ተነሳሽነትና ፈቃደኝነት ደካማ ከጠንካራ በመቀናጀት ያላቸውን አቅም ተጠቅመው አቅም የጎደላቸውንና የስራ ዕድል የሌላቸውን ሰዎች በመቀበል ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸውን ተጠቅመው እየተደጋገፉና እየተረዳዱ በመስራት በጋራ ሰርተው በማምረት የጋራ ዕድገትን በማምጣት እኩል ተጠቃሚ ሆነው የሚኖሩ ናቸው፡፡ የማህበሩ ራዕይም የአባላትን እውቀትና ጉልበት በማስተባበር፣ ደካማ ከጠንካራ በመደጋገፍ፣ አዳዲስ የስራ ዘርፎችን በመፍጠር የማህበሩን የኢኮኖሚ አቅም ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሳድጎና የአባላቱን እኩል ተጠቃሚነት አረጋግጦ ለሌላው ህብረተሰብ ምሳሌ በመሆን መኖር ነው፡፡

    የአውራ አምባ ማህበረሰብ ህብረት ስራ ማህበር አቅም ያጠራቸውንና ስራ ያጡ አካላትን በማካተት እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ከሚሰጠው ማህበራዊ ፋይዳ ባለፈ ለወገን ደራሽ በጎ አድራጎት ማህበርን በማቋቋም በችግር ለተጋለጡ አካላት ሰፊ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የበጎ አድራጎት ማህበሩ የገቢ ምንጭም የማህበሩ አባላት በየሳምንቱ አንዴ በልማት ስራ ተሳትፈው ከሚያገኙት ገቢና ማህበረሰቡን ለመጎብኘት ከሚመጡት ጎብኚዎች የሚገኝ የጉብኝት መግቢያ ክፍያ ገቢ ነው፡፡ ይህ የሚሰባሰበው ገቢም ለወገን ደራሽ ይባላል፡፡

    የወገን ደራሽ የሚውለው አሳዳጊ የሌላቸውን ልጆች ተንከባክቦ በማስተማር ለቁም ነገር ለማድረስ፣ ሲሰሩ ኖረው አገልግሎታቸውን የጨረሱ አረጋዊያንንና ታክሞ በማይድን የጤና ችግር ምክንያት መስራት የተሳናቸውን ወገኖች በመንከባከብ ቀሪ ህይወታቸውን ተደስተው እንዲያሳልፉ ለማድረግ፣ ታመው መታከሚያ ያጡ ወገኖችን በመደጎም ታክመው እንዲድኑ ለማድረግ፣ ወላጆቻቸው የትምህርት ወጫቸውን መሸፈን ለማይችሉ ተማሪዎች የት/ት ወጮቻቸውንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመደጎም ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ፣ የሚበላና የሚጠጣ ለቸገራቸው ወገኖች የገጠማቸውን ችግር ለመካፈል፣ ድንገተኛ አደጋ የገጠማቸውን ወገኖች በማገዝ ችግራቸውን ለመካፈል፣ የስራ ፈጠራ አቅም ኖሯቸው በገንዘብ ችግር ምክንያት ወደ ስራ ያልገቡ ወጣቶችን በመደገፍ የፈጠራ ስራቸውን ቀጥለው ህብረተሰቡን በፈጠራ ስራቸው እንዲጠቅሙ ለማበረታታትና እንዲሁም ለአካባቢው ህብረተሰብ ጠቃሚ በሆኑ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለመስራት ነው፡፡

    የአውራ አምባ ማህበረሰብ የሚመራው የክብር ዶ/ር ዙምራ ያነሳቸውን ጥቅል መሰረታዊ ሀሳቦች መሰረት በማድረግ ሲሆን ለስራ ያመቸው ዘንድ እሚመራውም 12 ኮሚቴዎችን አዋቅሮና አደራጅቶ ነው፡፡ እያንዳንዱ ኮሚቴ የራሱ አባላትና የስራ ድርሻ አለው፡፡ ከ12 ኮሚቴዎች መካከል አብይ ኮሚቴው የልማት ኮሚቴ የሚባል ሲሆን በአጠቃላይ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚካሄዱትን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎችና የሌሎቹን (የ11ዱን ንዑሳን ኮሚቴዎች) የስራ እንቅስቃሴዎቻቸውን ይከታተላል፤ ያስተባብራልም፡፡ ማህበረሰቡ የሚመራበትን ረቂቅ ደንብ ያወጣል፤ ያወጣውን ረቂቅ ደንብም በማህበረሰቡ አባላት በማጸደቅ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡

    እነዚህን የተለያዩ አደረጃጀቶች የሚመሩ መሪዎች በጠቅላላ አባላቱ ተሳትፎ በሀሳብ የበላይነት ይመረጣሉ፡፡ ለመሪነት በእጩነት የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎችም በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው፣ የማህበረሰቡን መርሆዎች በሙሉ እምነት የተቀበሉና ያንን ለማስፈፀም የሚተጉ፣ አስተዋይ የሆኑ፣ የተሻለ ዕውቀትና ጥሩ ስነምግባር የተላበሱ፣ የተጣለባቸውን አደራም በትክክል ለመወጣት ሙሉ ፈቃድና ቁርጠኝነት ያላቸው ናቸው፡፡ በዚህ የምርጫ ሂደት ያለፉ መሪዎችም ማህበረሰቡ ያወጣቸውንና የሚያወጣቸውን መርሆዎች መሰረት በማድረግ የተጣለባቸውን አደራ ከራሳቸው በላይ አድርገው በታማኝነትና በቅንነት የአባላቱን ጥያቄ እያሟሉ፣ ለሰዎች የሚመቸውን እያሰቡና መሆን እሚገባውን ሁሉ እያደረጉ ማህበረሰቡን ይመራሉ፡፡ አባላቱና መሪዎቹ ማንኛውንም የሚሰሯቸውን ስራዎች እሚሰሩት ተማምነው፣ ተሳስበውና እጅና ጓንት ሆነው ነው፡፡ ኃላፊዎች በሚተካኩ ጊዜም ተተኪው ራሱን ችሎ የመሪነት ስራውን እስኪለምደው ድረስ ከቀድሞው መሪ ጋር እጅና ጓንት ሆነው የአሰራር ልምዶችን ሲወስድ ይቆያል፡፡ ከዚያም የቀድሞውን መሪ በአማካሪነት ይዞና የአመራርነት ልምዶችን የእሱም ሀብት አድርጎ በመጠቀም ብልሽቶቹን ብቻ እያረመ መልካም ስራዎችን እያጠናከረና የራሱንም መልካም ስራዎች እየጨመረባቸው በመሄድ የመሪነት ኃላፊነትን እየተወጣ ይሄዳል፡፡

    በዚህ አደረጃጀትና አመራር እሚመራው የአውራ አምባ ማህበረሰብ የጠንካራ የስራ ባህል ባለቤት ነው፡፡ ማህበረሰቡ ይህን ጠንካራ የስራ ባህል ያዳበረውም አባላቱ የአብሮነት ኑሯቸውን ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ስራ ወዳድና ለስራ ጥሩ ተነሳሽነትን የተላበሱ በመሆናቸው፣ ስራቸውን በዕቅድ ስለሚመሩ፣ በዕቅድ ካስቀመጡት የስራ ሰዓት በላይ ለመስራት ከፍተኛ ቁርጠኝነት ስላላቸው፣ የስራ ሰዓትን በአግባቡ አክብረው ወደ ስራ የመሰማራት ልምድ በማዳበራቸው፣ ጥሩ የስራ ስነ-ምግባርን የተላበሱ በመሆናቸው፣ ለስራቸው ልዩ ክብር ስለሚሰጡ፣ ስራቸውን ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት ስለሚያደርጉ፣ አዲስ ስራን ለመፍጠር ጥሩ ተነሳሽነት ያላቸው በመሆናቸውና የስራ ውጤታቸውንም ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው በመሆናቸው ነው፡፡

    በማህበረሰቡ ሴቶች ከወንዶች ጋር ያላቸው የእኩልነት መብት ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ ነው፡፡ ሴቶች በትምህርት ተሳትፎ፣ እቤት ውስጥ በሚሰሩ ስራዎችና እንዲሁም በሌሎች በሚሰማሩበት የስራ ዓይነት፣ ንብረትን በማስተዳደር፣ እኩል ተወያይቶ ውሳኔ በመስጠት፣ በተለያዩ የማህበረሰቡ አደረጃጀቶች በመሳተፍና በማንኛውም እንቅስቃሴ ከወንዶች ጋር እኩል ተሳታፊ ሆነው የእኩልነት መብታቸው ተጠብቆና ተከብሮ ነው የሚኖሩት፡፡

   የአውራ አምባ ማህበረሰብ የልጆች መብትም እንዲሁ በተገቢው መንገድ ተከብሮ እንዲሄድ ነው እየተደረገ እሚገኘው፡፡ ልጆች በጥሩ ስነ-ምግባርና በትምህርት ተኮትኩተው ስለሚያድጉ በደባል ሱሶች፣ ባልተገባ ፆታዊ ግንኙነት፣ በዘረኝነት፣ በአድሎአዊነት፣ ከስርዓት አልበኝነት፣ ከስራ አጥነት እና በሌሎችም ለስራና ለአገር ዕድገት ፀር በሆኑ መጥፎ ልማዶች ነፃ ናቸው፡፡ የተሻለ ስራ ካላገኘን ብለው ጊዜያቸውን በዋዛና በፈዛዛ ለማሳለፍ አይሞክሩም፡፡ የተሻለ የስራ ዘርፍ እስከሚያገኙ በማንኛውም ስራ በመሰማራት ራሳቸውን ይመራሉ፡፡ ቤተሰቦቻቸውንም ይደግፋሉ፡፡ ስለሆነም በአውራ አምባ ማህበረሰብ እሴቶች ታንፀው ያደጉ ወጣቶች ታማኝ፣ የሰው ልጆችን ሰው በመሆናቸው ብቻ ወንድም እህት በማድረግ የሚያዩ፣ ጠብ የማያውቁ፣ ሰላማዊና ለስራ ታታሪ የሆኑ ወጣቶች ናቸው፡፡

    ማህበረሰቡ የተበጣጠሰ ወገንተኝነትን (ባዕድ-ዘመድ፣ ጎሳ፣ ነገድ፣ ብሄር፣ ወዘተ የሚሉትን ልዩነቶች) ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ሁሉንም የሰው ልጆች ሰው በመሆናቸው ብቻ ያለምንም ልዩነት ጥቅል ወገንተኝነትን መስርቶና ሁሉንም ዘመድ አድርጎ ነው እየኖረ እሚገኘው፡፡ ማህበረሰቡ ሁሉምን የሰው ልጆችን ዘመዱ አድርጎ እሚኖረውም ለሁሉም የሰው ልጆች ያለምንም ልዩነት እኩል ክብር ሰጥቶ፣ ደካማን ደግፎ፣ ለራሱ እንዲሆንለት እሚፈልገውን ለሌላውም እንዲሆንለት አድርጎ፣ በራሱ ላይ እንዲሆን እማይፈልገውን በሌሎች ላይ እንዳይደርስ አርቆ አስወግዶና ሙሉ ሰላምን ዘርግቶ በመሄድ ነው፡፡

    የአውራ አምባ ማህበረሰብ በአባላቱ መካከል ሙሉ ሰላምን በስራ ላይ በማዋል ለሰው ልጆች ሙሉ ክብርና ዘላቂነት ያለው ሰላም በመፍጠር ምሳሌ ሆኖ ይገኛል፡፡ ማህበረሰቡ የሰላም ተምሳሌት ለመሆን የበቃውም በማህበረሰቡ ምንም ዓይነት እንከን ሳይፈጠር ቀርቶ ሳይሆን በአባላቱ መካከል አንዳንድ በንግገር መተላለፍ (አለመግባባት) ቢከሰቱ ለዚህ መፍቻ የሚሆነውን ቁልፍ በአግባቡ መጠቀም በመቻሉ ነው፡፡ የችግር መፍቻ እንዲሆነው አድርጎ የተጠቀመው ቁልፍም ውይይት ነው፡፡ ማህበረሰቡ በውይይት ችግሮችን የሚፈታውም ዕለት በዕለት ችግሮች በሚፈጠሩ ጊዜ በሚደረግ የርስ- በርስ ውይይት፣ በየአስራ አምስት ቀኑ አንዴ በሚደረግ የቤተሰብ ውይይት፣ ሶስተኛ ወገንን (ቅሬታ ሰሚ) በመጠቀም በሚደረግ ውይይትና በወር አንዴ በሚደረግ ጠቅላላ የአባላት ውይይት ነው፡፡ ማህበረሰቡ እነዚህን የተለያዩ የውይይት ሂደቶችን ተጠቅሞ በመወያየት ሰላምን የሚያናጉ አሉባልታዎች ወይም ሀሜቶች ቢኖርሩ የአሉባልታዎችን ምንጭ አጣርቶ በመድረስ ከምንጫቸው አድርቆ ችግሮችን እየፈታ መሄድ በመቻሉ ነው በአባላቱ መካከል ሙሉ ሰላምን አረጋግጦና የሰላም ተምሳሌት ሆኖ እሚኖረው፡፡

    በማህበረሰቡ ጋብቻ የሚፈጸመው በሁለቱ ተቃራኒ ፆታዎች ሙሉ ፈቃደኝነት ሲሆን ጋብቻ የሚመሰረትበት ዝቅተኛው የዕድሜ ገደብ ደግሞ ለወንዱ 20 ዓመትና ለሴቷ 19 ዓመት ነው፡፡ ጋብቻ ከተፈጸመ በኋላ ሁለቱም ተጋቢዎች በተለመደው የስራ እንቅስቃሴያቸው ተሰማርተው ይውላሉ፡፡ በጋብቻ የሚባክን ቅንጣት ታክል ጊዜም ሆነ ለሰርግ ተብሎ የሚወጣ ምንም ዓይነት ወጭ የለም፡፡ ለሰርግ ተብሎ ይወጣ የነበረው ገንዘብ ለባለትዳሮቹ ጎጆ መውጫ እንዲውል ነው እሚደረገው፡፡ ከጋብቻ በፊት ወንዱም ሴት፣ ሴቷም ወንድ አያውቁም፡፡ ከትዳር በኋላም ከትዳር ጓዶቻቸው ውጭ ፈጽሞ አይሔዱም፡፡ 

    በአውራ አምባ ማህበረሰብ ሀዘን ማለት ሰዎች በህይወት እያሉ በሰዎች መካከል ሆነው ችግር እንዳይገጥማቸው መጠበቅና ገጥሟቸው ከተገኘም ለችግራቸው ዋስትና በመሆን ደስታቸውንም ሆነ ችግራቸውን በጋራ በመካፈል ሰዎቹ ከገጠማቸው ችግር መታደግ መቻል ማለት ነው፡፡ ከአቅም በላይ ሆኖ  አንድ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ከውስጥ የመነጨ ስሜት ነውና እንባ ማፍሰስ አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወዮ እያሉ፣ ደረትን እየደቁ፣ ፊትን እየነጩ ሙሾ በመደርደር ማልቀሱ የሞተውን ወገን አይተካም፡፡ እንዲያውም ይህን ማድረጉ በማይገኝ ነገር ጊዜን፣ ጉልበትንና ሀብትን ማባከንና ጤንነትን መጉዳት ነው በማለት በማህበረሰቡ የተንዛዛና የተራዘመ የለቅሶ ስርዓት የለም፡፡ የቀብሩ ስነ-ስርዓቱ የሚፈፀመውም ስነስርዓቱን ለመፈጸም ይበቃሉ በተባሉ ሰዎች ነው፡፡ የቀብር ስነስርዓቱ በክብር ከተጠናቀቀ በኋላ ሀዘኑ ያበቃል፡፡ በነጋተው የሟቹ ቤተሰቦች ይሰራሉ ተብለው ሳይሆን ከስራ ጓዶቻቸው ጋር ሆነው ሀዘኑን እንዲረሱት ወደ መደበኛ ስራቸው ያመራሉ፡፡